1 ነገሥት 3:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርሷ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጇን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጐኔ አስተኛችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ስለዚህም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፣ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ ልጄን ከአጠገቤ ወሰደችው፤ ከዚያም የእኔን ልጅ ራሷ ታቅፋ፣ የሞተ ልጇን አምጥታ በዕቅፌ አደረገችው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ተኝቼ ሳለሁ ሌሊት ተነሥታ ታቅፌው የተኛሁትን ልጄን ወስዳ በእርስዋ አልጋ ላይ ካስተኛች በኋላ የሞተውን ልጅዋን አምጥታ በእኔ አልጋ ላይ በጐኔ አስተኛችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እርስዋም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፥ እኔ አገልጋይህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከብብቴ ወሰደች፤ በብብቷም አስተኛችው፤ የሞተውንም ልጅዋን በእኔ ብብት አስተኛችው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እርስዋም በእኩለ ሌሊት ተነሥታ፥ እኔ ባሪያህ ተኝቼ ሳለሁ፥ ልጄን ከአጠገቤ ወሰደች፤ በብብትዋም አደረገችው፤ የሞተውንም ልጅዋን በእኔ ብብት አደረገች። |