1 ነገሥት 3:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእነርሱም አንደኛይቱ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ሆይ! ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን ስንኖር በዚያው በምንኖርበት ቤት ወንድ ልጅ ወለድኩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከእነርሱም አንዲቱ እንዲህ አለች፣ “ጌታዬ ሆይ፤ ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት ዐብረን እንኖራለን፤ ዐብራኝ እያለችም እኔ ልጅ ወለድሁ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከእነርሱም አንደኛይቱ እንዲህ አለች፤ “ንጉሥ ሆይ! ይህች ሴትና እኔ በአንድ ቤት አብረን ስንኖር በዚያው በምንኖርበት ቤት ወንድ ልጅ ወለድኩ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አንደኛዪቱም ሴት አለች፥ “ጌታዬ ሆይ! ስማኝ፥ እኔና ይህች ሴት በአንድ ቤት እንኖራለን፤ በአንድ ቤትም ወለድን። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አንደኛይቱም ሴት አለች “ጌታዬ ሆይ! እኔና ይህች ሴት በአንድ ቤት እንኖራለን፤ እኔም ከእርስዋ ጋር በቤት ሳለሁ ወለድሁ። |