እርሱም “ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሻግ ተብላ የምትጠራውን ሹኔማይት ልጃገረድ በሚስትነት እንዲድርልኝ እባክሽ አማልጅኝ” አላት።
1 ነገሥት 2:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እርሷም “መልካም ነው! ይህን ለንጉሡ እነግርልሃለሁ” አለችው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቤርሳቤህም፣ “መልካም ነው፤ ይህንኑ ለንጉሡ እነግርልሃለሁ” ብላ መለሰች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እርስዋም “መልካም ነው! ይህን ለንጉሡ እነግርልሃለሁ” አለችው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቤርሳቤህም፥ “መልካም ነው፤ ስለ አንተ ለንጉሡ እነግረዋለሁ” አለች። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ቤርሳቤህም “መልካም ነው፤ ስለ አንተ ለንጉሡ እነግረዋለሁ፤” አለች። |
እርሱም “ንጉሥ ሰሎሞን አንቺን እምቢ እንደማይልሽ ዐውቃለሁ፤ ስለዚህ አቢሻግ ተብላ የምትጠራውን ሹኔማይት ልጃገረድ በሚስትነት እንዲድርልኝ እባክሽ አማልጅኝ” አላት።
ስለዚህም ቤርሳቤህ የአዶንያስን ጉዳይ ልትነግር ወደ ንጉሡ ገባች፤ ንጉሡም ከተቀመጠበት ተነሥቶ እናቱን እጅ በመንሣት ተቀበላት፤ እርሱም በዙፋኑ ላይ ከተቀመጠ በኋላ ሌላ ዙፋን አስመጥቶ በቀኙ አስቀመጣት፤