እንግዲህ ሁለት ኰርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን በእሳት አያቀጣጥሉት፤ እኔም ሁለተኛውን ኰርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ።
1 ነገሥት 18:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፦ “ከጌታ ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዚያም ኤልያስ እንዲህ አላቸው፤ “ከእግዚአብሔር ነቢያት የተረፍሁ እኔ ብቻ ነኝ፤ በኣል ግን አራት መቶ ዐምሳ ነቢያት አሉት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኤልያስ እንዲህ አለ፦ “ከእግዚአብሔር ነቢያት የቀረሁት እኔ ብቻ ነኝ፤ አራት መቶ ኀምሳ የባዓል ነቢያት ግን እነሆ በዚህ አሉ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኤልያስም ሕዝቡን አለ፥ “ከእግዚአብሔር ነቢያት አንድ እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበዓል ነቢያት ግን አራት መቶ ሃምሳ ሰዎች ናቸው። የማምለኪያ ዐፀድ ነቢያትም አራት መቶ ናቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኤልያስም ሕዝቡን አለ “ከእግዚአብሔር ነቢያት እኔ ብቻ ቀርቻለሁ፤ የበኣል ነቢያት ግን አራት መቶ አምሳ ሰዎች ናቸው። |
እንግዲህ ሁለት ኰርማዎችን አምጡና የባዓል ነቢያት አንዱን ወስደው ይረዱት፤ ሥጋውንም ቆራርጠው እንጨት በመረብረብ በዚያ ላይ ያኑሩት፤ ነገር ግን በእሳት አያቀጣጥሉት፤ እኔም ሁለተኛውን ኰርማ ወስጄ እንደዚሁ አደርጋለሁ።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትህንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔንም እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ!” ሲል መለሰ።
ኤልያስም “ሁሉን የምትችል አምላኬ ሆይ! እኔ ለአምላክነትህ በመቅናት ዘወትር አንተን ብቻ አገለግላለሁ፤ የእስራኤል ሕዝብ ግን ከአንተ ጋር የገቡትን ቃል ኪዳን አፍርሰዋል፤ መሠዊያዎችህንም ሰባብረዋል፤ ነቢያትንም ሁሉ ገድለዋል፤ እነሆ እኔ ብቻዬን ቀርቻለሁ፤ እነርሱ ግን እኔን እንኳ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ” ሲል መለሰ።
በዚህን ጊዜ አንድ ነቢይ ወደ ንጉሥ አክዓብ ቀርቦ “ጌታ ‘ከቤንሀዳድ ሠራዊት ብዛት የተነሣ አትፍራ! እኔ ዛሬ በዚህ ሠራዊት ላይ ድልን እንድትቀዳጅ አደርጋለሁ፤ አንተም ደግሞ እኔ ጌታ መሆኔን ታውቃለህ’ ይልሃል” አለው።
ከዚህም በኋላ እነርሱ በወገባቸው ማቅ ታጥቀው፥ በራሳቸውም ገመድ ጠምጥመው ወደ ንጉሥ አክዓብ በመሄድ “አገልጋይህ ቤንሀዳድ ምሕረት አድርገህ ሕይወቱን እንድታተርፍለት ይማጠንሃል” አሉት። አክዓብም “እርሱ እስከ አሁን በሕይወት አለ ማለት ነውን? ከሆነስ መልካም ነው፤ እንግዲህ እርሱ ለእኔ እንደ ወንድም ነው!” ሲል መለሰላቸው።
የነቢያት ወገን የሆነ አንድ ነቢይ በጌታ ታዞ የእርሱ ጓደኛ የሆነውን ሌላ ነቢይ “ምታኝ!” አለው። ነቢዩ ግን እርሱን ለመምታት አልፈቀደም።