1 ነገሥት 18:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም “በእስራኤል ላይ ይህን ከባድ ችግር ያመጣህ አንተ ለካ እዚህ ነህን?” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜ፤ “እስራኤልን የምታውክ አንተ ነህን?” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም አክዓብ ኤልያስን ባየው ጊዜም “በእስራኤል ላይ ይህን ከባድ ችግር ያመጣህ አንተ ለካ እዚህ ነህን?” አለው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ፥ አክዓብ ኤልያስን፥ “እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አክዓብም ኤልያስን ባየው ጊዜ “እስራኤልን የምትገለባብጥ አንተ ነህን?” አለው። |
ሁሉም በእያንዳንዱ በፊቱ የነበረውን ሰው ገደለ፤ ሶርያውያንም ሸሹ፤ እስራኤልም አሳደዱአቸው፥ የሶርያም ንጉሥ የአዴር ልጅ በፈረሱ አመለጠ።
አለቆቹም ንጉሡን፦ “ይህን የመሰለውን ቃላት እየነገራቸው የሕዝቡን ሁሉ እጅ በዚህችም ከተማ የቀሩትን የወታደሮቹን እጅ እያደከመ ነውና ይህ ሰው እንዲገደል እንለምንሃለን፤ ይህ ሰው ክፋትን እንጂ ለዚህ ሕዝብ ሰላምን አይመኝለትምና” አሉት።
የቤቴልም ካህን አሜስያስ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ ኢዮርብዓም እንዲህ ብሎ ላከ፦ “አሞጽ በእስራኤል ቤት መካከል አሢሮብሃል፤ ምድሪቱም ቃሉን ሁሉ ልትሸከም አትችልም።
ባላገኙአቸውም ጊዜ ኢያሶንንና ከወንድሞች አንዳንዶችን ወደ ከተማው አለቆች ጎትተው “ዓለምን ያወኩ እነዚህ ወደዚህ ደግሞ መጥተዋል፥ ኢያሶንም ተቀብሎአቸዋል፤
ኢያሱም፦ “ለምን መከራን አመጣህብን? ጌታ ዛሬ መከራን ያመጣብሃል” አለው፤ እስራኤልም ሁሉ በድንጋይ ወገሩት፤ በእሳትም አቃጠሉአቸው፥ በድንጋይም ወገሩአቸው።