1 ዮሐንስ 3:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከመጀመሪያ የሰማችሁት መልእክት ይህ ነውና፥ እርሱም፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከመጀመሪያ የሰማችኋት፣ እርስ በርሳችን ልንዋደድ ይገባናል የምትለዋ መልእክት ይህች ናትና፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከመጀመሪያው የሰማችሁት መልእክት “እርስ በርሳችን እንፋቀር” የሚል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከመጀመሪያ የሰማችኋት መልእክት፦ እርስ በርሳችን እንዋደድ የምትል ይህች ናትና፤ |
ክርስቶስም እንዳፈቀራችሁ፥ ስለ እናንተም ለእግዚአብሔር መልካም መዓዛ ያለው መባንና መሥዋዕት አድርጎ ራሱን አሳልፎ እንደሰጠ፥ በፍቅር ተመላለሱ።
ወዳጆች ሆይ፥ ፍቅር ከእግዚአብሔር ስለ ሆነ፥ እርስ በርሳችን እንዋደድ፤ የሚያፈቅር ሁሉ ከእግዚአብሔር የተወለደ ነው፥ እግዚአብሔርንም ያውቃል።
አሁንም እመቤት ሆይ! አዲስን ትእዛዝ አልጽፍልሽም ነገር ግን ከመጀመሪያ ጀምሮ የነበረውን ነው፥ ይህም እርስ በእርሳችን እንድንዋደድ እለምንሻለሁ።