1 ቆሮንቶስ 6:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንግዲህ ለዚህ መሰል ጉዳይ ፍርድ ቢያስፈልጋችሁ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ እንዴት ታስቀምጣላችሁ? አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንግዲህ እንዲህ ያለ ጕዳይ ሲያጋጥማችሁ፣ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጅ አድርጋችሁ ሹሟ! አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንግዲህ እርስ በርሳችሁ ብትጣሉ ከክርስቲያናዊ ማኅበር ውጪ በሆኑትና በተናቁት ሰዎች ፊት ጉዳያችሁን እንዴት ታቀርባላችሁ? የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን የዚህ ዓለም ክርክር ያላቸው ሰዎች ቢኖሩ በቤተ ክርስቲያን የተሾሙ የበታች ወንድሞች ይስሙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንግዲህ ስለ ትዳር ጉዳይ የፍርድ ቤት ቢያስፈልጋችሁ በቤተ ክርስቲያን የተናቁትን ሰዎች ፈራጆች አድርጋችሁ ታስቀምጣላችሁን? |