1 ቆሮንቶስ 6:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአትን ይሠራል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚሠራው ኀጢአት ሁሉ ከአካሉ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ግን በገዛ አካሉ ላይ ኀጢአት ይሠራል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ስለዚህ ከዝሙት ራቁ፤ ሰው የሚያደርገው ሌላው ኃጢአት ሁሉ ከሰውነቱ ውጪ የሚደረግ ነው፤ ዝሙትን የሚፈጽም ሰው ግን በገዛ ሰውነቱ ላይ ኃጢአት ይሠራል፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከዝሙት ራቁ፤ ኀጢአት የሚሠራ ሰው ሁሉ ከሥጋው ውጭ ይሠራልና፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን ራሱ በሥጋው ላይ ኀጢአትን ይሠራል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል። |
ወይስ ዐመፀኞች የእግዚአብሔርን መንግሥት እንደማይወርሱ አታውቁምን? አትሳሳቱ፤ ሴሰኞች ቢሆኑ ወይም ጣዖትን የሚያመልኩ ወይም አመንዝሮች ወይም ግብረ ሰዶም የሚፈጽሙ፥
እንደገና ስመጣ በእናንተ ፊት አምላኬ ያዋርደኝ ይሆን እያልኩ፥ ከዚህ በፊት ስለ ሠሩት ኃጢአትና ስለ ፈጸሙትም ርኩሰት፥ ዝሙትና መዳራት ንስሓ ሳይገቡ ቀርተው እንዳላዝን እፈራለሁ።
እንግዲህ በእናንተ ያሉትን ምድራዊ ነገሮች ሁሉ ግደሉ፤ እነርሱም፦ “ዝሙትና ርኩሰት ፍትወትም ክፉ ምኞትም ጣዖትንም ማምለክ የሆነ ስግብግብነት” ናቸው፤