1 ቆሮንቶስ 6:16 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወይስ ከአመንዝራ ጋር የሚገናኝ አንድ አካል እንዲሆን አታውቁምን? “ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ፤” ተብሏልና። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወይስ ከዝሙት ዐዳሪ ጋራ የሚተባበር ሰው ከርሷ ጋራ አንድ ሥጋ እንደሚሆን አታውቁምን? “ሁለቱም አንድ ሥጋ ይሆናሉ” ተብሏልና። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከአመንዝራ ሴት ጋር የሚገናኝ ሰው ከእርስዋ ጋር አንድ አካል መሆኑን ታውቁ የለምን? “ሁለቱም አንድ አካል ይሆናሉ” ተብሎ ተጽፎአልና። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከአመንዝራ ጋር የተገናኘ ከእርስዋ ጋር አንድ አካል እንዲሆን አታውቁምን? መጽሐፍ፥ “ሁለቱ አንድ አካል ይሆናሉ” ብሎአልና። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወይስ ከጋለሞታ ጋር የሚተባበር አንድ ሥጋ እንዲሆን አታውቁምን? ሁለቱ አንድ ሥጋ ይሆናሉ ተብሎአልና። |
ከሦስት ወር በኋላ፥ “ምራትህ ትዕማር ዘማዊ ሆናለች፤ ከዚህም የተነሣ አርግዛለች” ተብሎ ለይሁዳ ተነገረው። ይሁዳም፥ “አውጧትና በእሳት ተቃጥላ ትሙት” አለ።