1 ቆሮንቶስ 14:5 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፥ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሁላችሁም በልሳን ብትናገሩ እወድዳለሁ፤ ከዚህ ይልቅ ግን ትንቢትን ብትናገሩ እወድዳለሁ። ቤተ ክርስቲያን እንድትታነጽ በልሳን የሚናገር ሰው የተናገረውን ካልተረጐመ፣ በልሳን ከሚናገር ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሁላችሁም በተለያዩ ቋንቋዎች ብትናገሩ እወድ ነበር፤ ይበልጥ የምወደው ግን ትንቢትን ብትናገሩ ነው፤ ማኅበረ ምእመናን እንዲታነጽ በተለያዩ ቋንቋዎች የተነገረውን የሚተረጒም ከሌለ፥ በተለያዩ ቋንቋዎች ከሚናገር ሰው ይልቅ ትንቢትን የሚናገር ሰው ይበልጣል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሁላችሁም በቋንቋ ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ይልቁንም ትንቢት ልትናገሩ እወዳለሁ፤ ሳይተረጕም በቋንቋ ከሚናገር ይልቅ ትንቢት የሚናገር እጅግ ይበልጣልና፤ ቢተረጕም ግን ማኅበሩን ያንጻል። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሁላችሁ በልሳኖች ልትናገሩ እወድ ነበር፥ ትንቢትን ልትናገሩ ግን ከዚህ ይልቅ እወዳለሁ፤ ማኅበሩ ይታነጽ ዘንድ ንግግሩን ባይተረጐም በልሳኖች ከሚናገር ትንቢትን የሚናገር ይበልጣል። |
ለሌላው ተአምራትን የማድረግ ኃይል ይሰጠዋል፤ ለሌላው ትንቢትን መናገር፥ ለአንዱ መናፍስትን መለየት፥ ለሌላው በልዩ ዓይነት ልሳን መናገር፥ ለሌላውም በልሳኖች የተነገረውን መተርጎም ይሰጠዋል፤