La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 12:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አንድ ብልት ቢሠቃይ፣ ብልቶች ሁሉ ዐብረው ይሠቃያሉ፤ አንድ ብልት ቢከብር፣ ሌሎቹም ብልቶች ዐብረው ደስ ይላቸዋል።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አንዱ የአካል ክፍል ሲሠቃይ ሌሎችም የአካል ክፍሎች በሙሉ አብረው ይሠቃያሉ፤ አንዱ የሰውነት ክፍል ሲከበር ሌሎቹም የሰውነት ክፍሎች አብረው ከእርሱ ጋር ይደሰታሉ።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

አንዱ የአ​ካል ክፍል ቢታ​መም ከእ​ርሱ ጋር የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ይታ​መ​ማሉ፤ አንዱ የአ​ካል ክፍል ደስ ቢለ​ውም የአ​ካል ክፍ​ሎች ሁሉ ከእ​ርሱ ጋር ደስ ይላ​ቸ​ዋል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

አንድም ብልት ቢሣቀይ ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሣቀያሉ፤ አንድ ብልትም ቢከበር ብልቶች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 12:26
9 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስ ግን “እንዲህ ጽድቅን ሁሉ መፈጸም ይገባናልና ለአሁን ፍቀድልኝ፤” ሲል መለሰለት፥ ያንጊዜ ፈቀደለት።


ቀኝ ዐይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።


ይህም በአካል ክፍሎች መካከል መለያየት ሳይኖር እርስ በርሳቸው እንዲተሳሰቡ ነው።


እናንተም የክርስቶስ አካል ናችሁ፤ እያንዳንዳችሁም የአካሉ ክፍሎች ናችሁ።


የእርስ በርሳችሁን ሸክም ተሸከሙ፥ በዚህም የክርስቶስን ሕግ ትፈጽማላችሁ።


እስረኞችን አብራችኋቸው እንደታሰረ ሆናችሁ አስቡ፤ እናንተም በሥጋ እንዳለ እያሰባችሁ የተጨነቁትንም እንደራሳችሁ አስቡ።


በመጨረሻም ሁላችሁ በአንድ ልብ ሁኑ፤ እርስ በእርሳችሁ ተሳሰቡ፤ በወንድማማችነት ፍቅር ተዋደዱ፤ ርኅሩኆችና ትሑታን ሁኑ።