La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




1 ቆሮንቶስ 12:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

ፊት ለፊት ለሚታዩት የአካላችን ክፍሎች ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። እግዚአብሔር ግን ለማየት የሚያሳፍሩ መስለው የሚታዩንን የአካል ክፍሎች በበለጠ ክብር እንዲያዙ አድርጎ የአካል ክፍሎችን አስማምቷል።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

የማናፍርባቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። እግዚአብሔር ግን የአካል ብልቶችን አንድ ላይ አገጣጥሞ ክብር ለሚጐድላቸው የበለጠ ክብር ሰጥቷቸዋል፤

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ፊት ለፊት ለሚታዩት የአካል ክፍሎች ግን ይህ ሁሉ አያስፈልጋቸውም፤ እግዚአብሔር ግን ለማየት የሚያሳፍሩ መስለው የሚታዩንን የአካል ክፍሎች በበለጠ ክብር እንዲያዙ አድርጎ የአካል ክፍሎችን አገጣጥሞአል።

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ለከ​በ​ረው የአ​ካ​ላ​ችን ክፍል ክብ​ርን አን​ሻ​ለ​ትም፤ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግን ሰው​ነ​ታ​ች​ንን አስ​ማ​ም​ቶ​ታል፤ ይል​ቁ​ንም ታና​ሹን የአ​ካል ክፍል አክ​ብ​ሮ​ታል።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ክብር ያላቸው ብልቶቻችን ግን ይህ አያስፈልጋቸውም። ነገር ግን ብልቶች እርስ በርሳቸው በትክክል ይተሳሰቡ ዘንድ እንጂ በአካል መለያየት እንዳይሆን፥ ለጎደለው ብልት የሚበልጥ ክብር እየሰጠ እግዚአብሔር አካልን አገጣጠመው።

Ver Capítulo



1 ቆሮንቶስ 12:24
5 Referencias Cruzadas  

አዳምና ሚስቱ ሁለቱም ራቁታቸውን ነበሩ፥ አይተፋፈሩምም ነበር።


እግዚእብሔርም፦ “ዕራቁትህን እንደሆንህ ማን ነገረህ? እንዳትበላ ካዘዝሁህ ዛፍ በውኑ ከእርሱ በላህን?” አለው።


ቀኝ ዐይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና።


ከአካልም ክፍሎች ያልከበሩ ሆነው የሚመስሉንን በሚበዛ ክብር እናለብሳቸዋለን፤ በምናፍርባቸውም የአካላችን ክፍሎች ክብር ይጨመርላቸዋል፤


ይህም በአካል ክፍሎች መካከል መለያየት ሳይኖር እርስ በርሳቸው እንዲተሳሰቡ ነው።