1 ዜና መዋዕል 5:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጋድም ልጆች ከሮቤል ነገድ አጠገብ ባለው በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ ተቀመጡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጋድ ነገድ ደግሞ ከእነርሱ ቀጥሎ እስከ ሰልካ ድረስ በሚገኘው በባሳን ምድር ኖሩ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የጋድ ነገድ፥ የሮቤል ነገድ ከሚኖሩበት በስተ ሰሜን ባለው ምድር ይኖሩ ነበር፤ ይህም ምድር በባሳን ውስጥ ሲሆን በስተ ምሥራቅ እስከ ሳለካ ይደርሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጋድም ልጆች በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በአፋዛዣቸው ተቀመጡ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) የጋድም ልጆች በባሳን ምድር እስከ ሰልካ ድረስ በፊት ለፊታቸው ተቀመጡ። |
ይገዛ የነበረው የአርሞንዔምን ተራራ፥ ሰልካን፥ ባሳንንም ሁሉ እስከ ጌሹራውያንና እስከ ማዕካታውያን ዳርቻ፥ የገለዓድንም እኩሌታ እስከ ሐሴቦን ንጉሥ እስከ ሴዎን ዳርቻ ድረስ ነበር።