እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
1 ዜና መዋዕል 16:18 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲህም አለ፦ “ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ድርሻ እሰጣለሁ፤” አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲህ ሲል፣ “የርስትህ ድርሻ አድርጌ፣ የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ይህም ቃል ኪዳን፥ “የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ፤ ለአንተም የተመደበ ርስትም ይሆናል” የሚል ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እንዲህም አለ፥ “ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እንዲህም አለ “ለአንተ የከነዓንን ምድር የርስታችሁን ገመድ እሰጣለሁ፤” |
እግዚአብሔርም ለአብራም ተገለጠለትና፦ ይህችን ምድር ለዘርህ እሰጣለሁ አለው። እርሱም ለተገለጠለት ለእግዚአብሔር በዚያ ስፍራ መሠውያን ሠራ።
በእንግድነት የምትኖርባትን ምድር፥ የከነዓን ምድር ሁሉ፥ ለዘለዓለም ግዛት ይሆንህ ዘንድ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ እሰጣለሁ፥ አምላክም እሆናቸዋለሁ።”