1 ዜና መዋዕል 13:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ዘንድ ቅን ነበረና ጉባኤው ሁሉ፦ “እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ስላገኘ መላው ማኅበር ይህንኑ ለማድረግ ተስማማ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሕዝቡም በሐሳቡ ደስ በመሰኘት ተስማሙ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ዘንድ ቅን ነበረና የእስራኤል ጉባኤ ሁሉ፥ “እንዲሁ እናደርጋለን” አሉ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገሩም በሕዝቡ ሁሉ ዐይን ዘንድ ቅን ነበረና ጉባኤው ሁሉ “እንዲሁ እናደርጋለን፤” አሉ። |