1 ዜና መዋዕል 12:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እነዚህ የጋድ ልጆች የሠራዊቱ አለቆች ነበሩ፤ ከእነርሱም ታናሹ የመቶ አለቃ፥ ታላቁ የሺህ ማዕርግ ያላቸው ነበሩ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እነዚህ ጋዳውያን የጦር አዛዦች ነበሩ፣ ከእነርሱ ታናሽ የሆነው እንደ መቶ፣ ታላቅ የሆነው ደግሞ እንደ ሺሕ አለቃ ይቈጠር ነበር። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከጋድ ነገድ ከሆኑት ከእነዚህ ሰዎች መካከል ጥቂቶቹ የሺህ አለቅነት ማዕርግ ያላቸው የበላይ መኰንኖችና የመቶ አለቅነት ማዕርግ ያላቸው የበታች መኰንኖች ነበሩ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እነዚህ የጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች ነበሩ፤ ከእነርሱም ታናሹ የመቶ አለቃ ታላቁ የሺህ አለቃ ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እነዚህ የጋድ ልጆች የጭፍራ አለቆች ነበሩ፤ ከእነርሱም ታናሹ ከመቶ፥ ታላቁ ከሺህ ይመዛዘኑ ነበር። |