ስለዚህም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ “ይህ ነገር ደም ነው! የሦስቱ ጠላቶቻችን ሠራዊቶች እርስ በርሳቸው በመተራረድ ተላልቀዋል! እንግዲህ ሄደን ሰፈራቸውን እንዝረፍ!” ተባባሉ።
1 ዜና መዋዕል 10:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በማግስቱም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በማግስቱ ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ ሲመጡ፣ ሳኦልና ልጆቹ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኟቸው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በጦርነቱ ማግስት ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን እስራኤላውያን ለመግፈፍ በሄዱ ጊዜ የሳኦልና የልጆቹ ሬሳ በጊልቦዓ ተራራ ላይ ተጋድሞ አገኙ፤ የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነጋውም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጌላቡሄ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በነጋውም ፍልስጥኤማውያን የሞቱትን ለመግፈፍ በመጡ ጊዜ ሳኦልንና ልጆቹን በጊልቦዓ ተራራ ላይ ወድቀው አገኙአቸው። |
ስለዚህም ድምፃቸውን ከፍ አድርገው በመጮኽ “ይህ ነገር ደም ነው! የሦስቱ ጠላቶቻችን ሠራዊቶች እርስ በርሳቸው በመተራረድ ተላልቀዋል! እንግዲህ ሄደን ሰፈራቸውን እንዝረፍ!” ተባባሉ።
በሸለቆውም የነበሩት የእስራኤል ሰዎች ሁሉ ሠራዊቱ እንደ ሸሸ፥ ሳኦልና ልጆቹም እንደሞቱ ባዩ ጊዜ ከተሞቻቸውን ለቅቀው ሸሹ፤ ፍልስጥኤማውያንም መጥተው ተቀመጡባቸው።
ኢዮሣፍጥና ሕዝቡም ምርኮ ለመውሰድ መጡ፤ ብዙ ከብትና ልዩ ልዩ ዕቃም፥ ልብስም፥ እጅግም ያማረ ዕቃ አገኙ፥ በዘበዙትም፥ ሁሉንም ለመሸከም አልቻሉም፤ ከምርኮውም ብዛት የተነሣ እስከ ሦስት ቀን ድረስ ይበዘብዙ ነበር።