ኢያሱ 9:2 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱንና እስራኤልን ለመውጋት በአንድነት መጡ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱንና እስራኤልን ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ኀይላቸውን በአንድነት አስተባብረው በኢያሱና በእስራኤላውያን ላይ ለመዝመት መጡ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱንና እስራኤልን ሁሉ ሊወጉ አንድ ሆነው ተሰበሰቡ። |
አምስቱም የአሞራውያን ነገሥታት፥ የኢየሩሳሌም ንጉሥ፥ የኬብሮን ንጉሥ፥ የየርሙት ንጉሥ፥ የለኪሶ ንጉሥ፥ የአዶላም ንጉሥ፥ ከሠራዊቶቻቸው ሁሉ ጋር ተሰብስበው ወጡ፥ ከገባዖንም ጋር ሊጋጠሙ ከበቡአት።
ዮርዳኖስንም ተሻገራችሁ፥ ወደ ኢያሪኮም መጣችሁ፥ የኢያሪኮም ሰዎች፥ አሞራዊው፥ ፌርዛዊው፥ ከነዓናዊው፥ ኬጢያዊው፥ ጌርጌሳዊው፥ ኤዊያዊው፥ ኢያቡሳዊው ተዋጉአችሁ፥ አሳልፌም በእጃችሁ ሰጠኋቸው።
ምልክት እያደረጉ የአጋንንት መናፍስት ናቸውና፥ በታላቁም ሁሉን በሚገዛ በእግዚአብሔር ቀን ወደ ሚሆነው ጦር እንዲያስከትቱአቸው ወደ ዓለም ሁሉ ነገሥታት ይወጣሉ።