La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ኢያሱ 4:3 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሡ፥ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው ብለህ እዘዛቸው አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እንዲሁም ከዮርዳኖስ ወንዝ መካከል ልክ ካህናቱ ከቆሙበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋይ አንሥተው በመሸከም ከእናንተ ጋራ እንዲሻገሩና ዛሬ በምታድሩበት ቦታ እንዲያኖሯቸው ንገራቸው።”

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እንዲህም ብለህ እዘዛቸው፦ ‘በዮርዳኖስ መካከል የካህናት እግር ከቆመበት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሡ፤ ተሸክማችሁም በዚህ ሌሊት በምታድሩበት ስፍራ አኑሩአቸው።’”

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

በዮርዳኖስ ወንዝ መካከል፥ ካህናቱ ከቆሙበት ከዚያው ስፍራ ዐሥራ ሁለት ድንጋዮች ይዘው እንዲወጡ እዘዛቸው፤ ድንጋዮቹንም ወስደው ዛሬ ማታ በምትሰፍሩበት ስፍራ ያቆሙአቸው ዘንድ ንገር።”

Ver Capítulo

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በዮ​ር​ዳ​ኖስ መካ​ከል የካ​ህ​ናት እግር ከቆ​መ​በት ስፍራ ዐሥራ ሁለት ቀላል ድን​ጋ​ዮ​ችን እን​ዲ​ያ​ነሡ እዘ​ዛ​ቸው፤ ከእ​ና​ን​ተም ጋር ውሰ​ዱ​አ​ቸው፤ ከዚ​ያም ሌሊት በም​ታ​ድ​ሩ​በት ቦታ በየ​ነ​ገ​ዳ​ችሁ ጠብ​ቋ​ቸው።”

Ver Capítulo



ኢያሱ 4:3
11 Referencias Cruzadas  

ለሐውልት የተከልሁት ይህም ድንጋይ የእግዚአብሔር ቤት ይሆናል ከሰጠኸኝም ሁሉ ለአንተ ከአሥር እጅ አንዱን እሰጥሃለሁ።


መልሶም፦ እላችኋለሁ፥ እነዚህ ዝም ቢሉ ድንጋዮች ይጮኻሉ አላቸው።


ኢያሱም ለሕዝቡ፦ እነሆ፥ የተናገረንን የእግዚአብሔርን ቃል ሁሉ ሰምቶአልና ይህ ድንጋይ ይመሰክርብናል፥ እንግዲህ አምላካችሁን እንዳትክዱ ይህ ምስክር ይሆንባችኋል አላቸው።


እንዲህም ይሆናል፥ የምድርን ሁሉ ጌታ የእግዚአብሔርን ታቦት የተሸከሙ ካህናት እግር ጫማ በዮርዳኖስ ውኃ ውስጥ ሲቆም፥ ከላይ የሚወርደው የዮርዳኖስ ውኃ ይቋረጣል፥ እንደ ክምርም ሆኖ ይቆማል።


ኢያሱም ከየነገዱ አንድ አንድ ሰው፥ ከእስራኤል ልጆች ያዘጋጃቸውን አሥራ ሁለት ሰዎች ጠራ።


የእስራኤልም ልጆች ኢያሱ እንዳዘዘ አደረጉ፥ እግዚአብሔርም ኢያሱን እንደ ተናገረው በእስራኤል ነገድ ቁጥር ከዮርዳኖስ መካከል አሥራ ሁለት ድንጋዮች አንሥተው ወደሚያድሩበት ስፍራ ወሰዱ፥ በዚያም አኖሩአቸው።


ሳሙኤልም አንድ ድንጋይ ወስዶ በምጽጳና በሼን መካከል አኖረው፥ ስሙንም፦ እስከ አሁን ድረስ እግዚአብሔር ረድቶናል ሲል አቤንኤዘር ብሎ ጠራው።