ኢያሱ 3:9 - መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፦ ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አለ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢያሱ የእስራኤልን ሕዝብ “ወደዚህ ቀርባችሁ፣ የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ አላቸው፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፦ “ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችሁን የጌታን ቃላት ስሙ” አለ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከዚህ በኋላ ኢያሱ እስራኤላውያንን፦ “ወደዚህ ቅረቡና የአምላካችሁን የእግዚአብሔርን ቃል አድምጡ” አላቸው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢያሱም ለእስራኤል ልጆች፥ “ወደዚህ ቀርባችሁ የአምላካችንን የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ” አለ። |
አሁንም፥ እስራኤል ሆይ፥ እንድታደርጉአቸው በሕይወትም እንድትኖሩ፥ የአባቶቻችሁም አምላክ እግዚአብሔር ወደሚሰጣችሁ ምድር ገብታችሁ እንድትወርሱ፥ የማስተምራችሁን ሥርዓትና ፍርድ ስሙ።
ኢያሱም አለ፦ ሕያው አምላክ በመካከላችሁ እንደ ሆነ፥ እርሱም ከፊታችሁ ከነዓናዊውን ኬጢያዊውንም ኤዊያዊውንም ፌርዛዊውንም ጌርጌሳዊውንም አሞራዊውንም ኢያቡሳዊውንም ፈፅሞ እንዲያወጣ በዚህ ታውቃላችሁ።