ወደ ዕረፍቴም እንዳይገቡ በቍጣዬ ማልሁ።
እግዚአብሔር የሰው ሐሳብ ከንቱ እንደ ሆነ ያውቃል።
የሰዎች ሐሳብ ከንቱ እንደሆነ ጌታ ያውቃል።
እግዚአብሔር የሰዎችን ሁሉ ሐሳብና፥ ከንቱነታቸውን ያውቃል።
“ሥራቸውንና አሳባቸውን ዐውቄአለሁ፤ እነሆም እኔ እመጣለሁ፤ አሕዛብንና ልሳናትንም ሁሉ እሰበስባለሁ፤ እነርሱም ይመጣሉ፤ ክብሬንም ያያሉ።
መጽሐፍ እንዲህ ብሎአልና፥ “እኔ የጥበበኞችን ጥበብ አጠፋለሁ፤ የመካሪዎችንም ምክር እንቃለሁ።”
ሰዎች በጥበባቸው በማያውቁት በእግዚአብሔር ጥበብ ስንፍና በሚመስላቸው ትምህርት ያመኑትን ሊያድናቸው እግዚአብሔር ወድዶአልና።
የእግዚአብሔር ስንፍና ከሰው ይልቅ ይጠበባልና፥ የእግዚአብሔርም ድካም ከሰው ይልቅ ይበረታልና።
ዳግመኛ “የጥበበኞች አሳብ ከንቱ እንደ ሆነ እግዚአብሔር ያውቃል” ብሎአል።