የምድር ነገሥታት ሁሉ ይሰግዱለታል ፥ አሕዛብም ሁሉ ይገዙለታል።
እነርሱም፣ “እግዚአብሔር ትቶታል፤ የሚያስጥለው የለምና፣ ተከታትላችሁ ያዙት” አሉ።
“እግዚአብሔር ትቶታል፥ የሚያድነው የለምና ተከትላችሁ ያዙት።”
“እግዚአብሔር ትቶታል፤ ተከታትለን እንያዘው፤ የሚያድነው ማንም የለም” ይላሉ።
ብዙ ሰዎች ነፍሴን አልዋት፦ “አምላክሽ አያድንሽም።”
ነፍሴን እንደ አንበሳ እንዳይነጥቋት፥ የሚያድንና የሚታደግ ሳይኖር።
በዘጠኝ ሰዓትም ኢየሱስ “ኤሎሄ ኤሎሄ ላማ ሰበቅታኒ?” ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህም “አምላኬ አምላኬ፥ ስለ ምን ተውኸኝ?” ማለት ነው።
ሌሎቹ ግን “ተው፤ ኤልያስ መጥቶ ያድነው እንደ ሆነ እንይ፤” አሉ።
ለሳኦልም ዳዊት ወደ ቂአላ እንደ መጣ ተነገረው፤ ሳኦልም፥ “መዝጊያና መወርወሪያ ወዳለባት ከተማ ገብቶ ተገኝቶአልና እግዚአብሔር በእጄ አሳልፎ ሰጥቶታል” አለ።