ዘኍል 7:36 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በአምስተኛውም ቀን የስምዖን ልጆች አለቃ የሲሩሳዴ ልጅ ሰላምያል መባውን አቀረበ፤ አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዐምስተኛው ቀን የስምዖን ሕዝብ አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በአምስተኛውም ቀን የስምዖን ልጆች አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል አቀረበ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በአምስተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከስምዖን ነገድ የጹሪሻዳይ ልጅ ሸሉሚኤል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በአምስተኛውም ቀን የስምዖን ልጆች አለቃ የሱሪሰዳይ ልጅ ሰለሚኤል፤ |
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የሴድዮር ልጅ የኤሊሱር መባ ይህ ነበረ።
መባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉ፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነ አንድ የብር ድስት፤