ዘኍል 7:18 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በሁለተኛውም ቀን የይሳኮር አለቃ የሰገር ልጅ ናትናኤል አቀረበ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም በሁለተኛው ቀን የይሳኮር አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል ስጦታውን አመጣ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በሁለተኛውም ቀን የይሳኮር አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል አቀረበ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በሁለተኛው ቀን መባውን ያቀረበው ከይሳኮር ነገድ የጹዓር ልጅ ናትናኤል ነበር። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) በሁለተኛውም ቀን የይሳኮር አለቃ የሶገር ልጅ ናትናኤል አቀረበ። |
ለደኅንነትም መሥዋዕት ሁለት ጊደሮች፥ አምስት አውራ በጎች፥ አምስት አውራ ፍየሎች፥ አምስት የአንድ ዓመት እንስት የበግ ጠቦቶች ነበረ፤ የአሚናዳብ ልጅ የነአሶን መባ ይህ ነበረ።
ለመባውም ለእህል ቍርባን በዘይት የተለወሰ መልካም ዱቄት የተሞሉትን፥ ሚዛኑ እንደ መቅደሱ ሰቅል ሚዛን መቶ ሠላሳ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ወጭት፥ ሚዛኑም ሰባ ሰቅል የሆነውን አንድ የብር ድስት፤