እናቱና ወንድሞቹም መጡ፤ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።
ከዚህ በኋላ እናቱና ወንድሞቹ መጡ፤ በውጭ ቆመውም ሰው ልከውበት አስጠሩት።
የኢየሱስ እናትና ወንድሞቹ ወደ እርሱ መጡ፤ በውጪም ቆመው ወደ እርሱ ሰው ላኩና አስጠሩት።
እናቱና ወንድሞቹም መጡ በውጭም ቆመው ወደ እርሱ ልከው አስጠሩት።
ዘመዶቹም ሰምተው “አበደ” ብለዋልና ሊይዙት ወጡ።
“ርኵስ መንፈስ አለበት፤” ይሉ ነበርና።
ብዙ ሰዎችም በዙሪያው ተቀምጠው ነበሩና “እነሆ፥ እናትህ ወንድሞችህም በውጭ ቆመው ይፈልጉሃል፤” አሉት።