La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




ማርቆስ 1:34 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፤ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

እርሱም በተለያየ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትም አወጣ፤ ነገር ግን አጋንንቱ የኢየሱስን ማንነት ያውቁ ስለ ነበር እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

እርሱም በተለያየ በሽታ የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትም አወጣ፤ ነገር ግን አጋንንቱ የኢየሱስን ማንነት ያውቁ ስለ ነበር እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

ኢየሱስ በልዩ ልዩ በሽታ የሚሠቃዩትን ብዙ ሰዎች ፈወሰ፤ ብዙ አጋንንትንም አስወጣ፤ አጋንንቱም እርሱ ማን እንደ ሆነ ያውቁ ነበር፤ ይሁን እንጂ ኢየሱስ እንዲናገሩ አልፈቀደላቸውም።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

በልዩ ልዩ ደዌም የታመሙትን ብዙዎችን ፈወሰ፥ ብዙዎችንም አጋንንት አወጣ፥ አጋንንትም ክርስቶስ መሆኑን አውቀው ነበርና ሊናገሩ አልፈቀደላቸውም።

Ver Capítulo



ማርቆስ 1:34
6 Referencias Cruzadas  

ኢየሱስም በምኩራቦቻቸው እያስተማረ የመንግሥትንም ወንጌል እየሰበከ በሕዝብም ያለውን ደዌና ሕማም ሁሉ እየፈወሰ በገሊላ ሁሉ ይዞር ነበር።


ዝናውም ወደ ሶርያ ሁሉ ወጣ፤ በልዩ ልዩ ደዌና ሥቃይም ተይዘው የታመሙትን ሁሉ አጋንንትም ያደሩባቸውን በጨረቃም የሚነሣባቸውን ሽባዎችንም ወደ እርሱ አመጡ፤ ፈወሳቸውም።


ኢየሱስም “ዝም በል፤ ከእርሱም ውጣ፤” ብሎ ገሠጸው።


እንዳይገልጡትም በጣም አዘዛቸው።


ብዙ አጋ​ን​ን​ትም፥ “አንተ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ልጅ ክር​ስ​ቶስ ነህ” እያ​ሉና እየ​ጮሁ ይወጡ ነበር፤ እር​ሱም ይገ​ሥ​ጻ​ቸው ነበር፤ ክር​ስ​ቶ​ስም እንደ ሆነ ያውቁ ነበ​ርና እን​ዲ​ና​ገሩ አይ​ፈ​ቅ​ድ​ላ​ቸ​ውም ነበር።