ሉቃስ 15:7 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኙ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በሰማያት ፍጹም ደስታ ይሆናል። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እላችኋለሁ፤ እንደዚሁም ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ፣ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁ ንስሓ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሓ በሚገባ በአንድ ኀጢአተኛ ምክንያት በሰማይ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ንስሓ መግባት ከማያስፈልጋቸው ዘጠና ዘጠኝ ደጋግ ሰዎች ይልቅ ንስሓ በሚገባ አንድ ኃጢአተኛ ምክንያት በሰማይ እንዲሁ ደስታ ይሆናል እላችኋለሁ።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል። |
እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሓ ስለሚገባ ስለ አንድ ኀጢኣተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በሰማያት ደስታ ይሆናል።”
መልሶም አባቱን እንዲህ አለው፦ ‘እነሆ፥ ይህን ያህል ዓመት ተገዛሁልህ፤ ፈጽሞ ከትእዛዝህ አልወጣሁም፤ ለእኔ ግን ከባልንጀሮች ጋር ደስ እንዲለኝ አንድ የፍየል ጠቦት እንኳ አልሰጠኸኝም።
ነገር ግን ይህ ወንድምህ ሞቶ ነበረ፤ ሕያው ሆኖአልና፥ ጠፍቶም ተገኝቶአልና፥ ደስ ሊለን፥ ሐሤትም ልናደርግ ይገባል።”
ወደ ቤቱም በገባ ጊዜ፥ ወዳጆቹንና ጎረቤቶቹን ጠርቶ፦ የጠፋችኝን በጌን አግኝቼአታለሁና ከእኔ ጋር ደስ ይበላችሁ ይላቸዋል።
“ዐሥር ድሪም ያላት ሴት ብትኖር፥ አንዲቱ ብትጠፋባት መብራት አብርታ በቤቷ ያለውን ሁሉ እየፈነቀለች እስክታገኛት ድረስ ተግታ ትፈልግ የለምን?
እርሱም፥ “እናንተስ ለሰው ይምሰል ትመጻደቃላችሁ፤ እግዚአብሔርም ልቡናችሁን ያውቃል፤ በሰው ዘንድ የከበረ በእግዚአብሔር ዘንድ የተናቀ ይሆናልና።