ሁሉም የንግግሩን መከናወን መሰከሩለት፤ የአንደበቱንም ቅልጥፍና እያደነቁ፥ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።
ዮሐንስ 7:46 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሎሌዎቻቸውም መልሰው፥ “ያ ሰው እንደ ተናገረው ያለ ከቶ ሰው አልተናገረም” አሉአቸው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ጠባቂዎቹም፣ “እንደዚህ ሰው፣ ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቅም” ሲሉ መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዘቦቹም “እንደዚህ ሰው ማንም ከቶ አልተናገረም፤” ብለው መለሱ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወታደሮቹም “ይህ ሰው እንደሚናገረው ዐይነት ማንም ተናግሮ አያውቅም” ሲሉ መለሱ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ሎሌዎቹ፦ “እንደዚህ ሰው ማንም እንዲሁ ከቶ አልተናገረም” ብለው መለሱ። |
ሁሉም የንግግሩን መከናወን መሰከሩለት፤ የአንደበቱንም ቅልጥፍና እያደነቁ፥ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።
እነሆ፥ እርሱ በገሀድ ይናገራል፤ እነርሱ ግን ምንም የሚሉት የለም፤ ይህ በእውነት ክርስቶስ እንደ ሆነ ምናልባት አለቆች ዐውቀው ይሆን?
ፈሪሳውያንም ሕዝቡ በእርሱ ምክንያት እንደ አጕረመረሙ ሰሙ፤ የካህናት አለቆችና ፈሪሳውያንም ይይዙት ዘንድ ሎሌዎቻቸውን ላኩ።