ዮሐንስ 7:27 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ነገር ግን ይህን ከየት እንደ ሆነ እናውቃለን፤ ክርስቶስ በሚመጣበት ጊዜስ ከወዴት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም”። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ይህ ሰው ግን ከየት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን፤ ክርስቶስ ሲመጣ እኮ ከየት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም።” መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሆኖም ይህ ሰው ከወዴት እንደሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደሆነ ማንም አያውቅም።” አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሆኖም ይህ ሰው ከወዴት እንደ ሆነ እኛ እናውቃለን፤ መሲሕ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደ ሆነ የሚያውቅ ማንም የለም።” መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ነገር ግን ይህን ከወዴት እንደ ሆነ አውቀናል፤ ክርስቶስ ሲመጣ ግን ከወዴት እንደ ሆነ ማንም አያውቅም።” |
“እነሆ ለዳዊት የጽድቅ ቍጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥” ይላል እግዚአብሔር፤ ንጉሥ ይነግሣል፤ ያስባል፤ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።
አለቃቸውም ከእነርሱ ውስጥ ይሾማል፤ ገዢአቸውም ከመካከላቸው ይወጣል፤ እሰበስባቸዋለሁ፤ ወደ እኔም እመልሳቸዋለሁ፤ ወደ እኔ ይመለስ ዘንድ ልብ የሰጠው ማን ነው? ይላል እግዚአብሔር።
አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ፥ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።
ይህስ ጸራቢው የማርያም ልጅ የያቆብም የዮሳም የይሁዳም የስምዖንም ወንድም አይደለምን? እኅቶቹስ በዚህ በእኛ ዘንድ አይደሉምን?” አሉ፤ ይሰናከሉበትም ነበር።
ሁሉም የንግግሩን መከናወን መሰከሩለት፤ የአንደበቱንም ቅልጥፍና እያደነቁ፥ “ይህ የዮሴፍ ልጅ አይደለምን?” ይሉ ነበር።
“እኛ አባቱንና እናቱን የምናውቃቸው ይህ የዮሴፍ ልጅ ኢየሱስ አይደለምን? እንግዲህ እንዴት ከሰማይ ወረድሁ ይለናል?” አሉ።