ዘፍጥረት 10:12 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) በነነዌና በካለህ መካከልም ዳስን ሠራ፤ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት። አዲሱ መደበኛ ትርጒም እንዲሁም በነነዌና በካለህ መካከል ሬስን ቈረቈረ፤ ታላቁንም ከተማ መሠረተ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከልም ሬሴን መሠረተ፥ እርሷም ታላቂቱ ከተማ ናት። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እንዲሁም በነነዌና በካላሕ መካከል ያለውን ታላቅ ከተማ ሬሴን የተባሉትን ከተሞች መሠረተ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ካለህን በነነዌና በካለህ መካከለም ሬሴንን ሠራ እርስዋም ታላቂቱ ከተማ ናት። |
“ሞሳሕና ቶቤል፥ ሠራዊታቸውም ሁሉ በዚያ አሉ፤ መቃብራቸውም በዙሪያቸው ነው፤ ሁሉም ሳይገረዙ በሰይፍ ተገድለዋል፤ በሕያዋን ምድር ያስፈሩ ነበርና።