እንዲሁም በሰሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎች፥ ሃያም እግሮች ይሁኑ፤ ለምሰሶዎችም በብር የተለበጡ ኩላቦችና ዘንጎች ይሁኑ።
ዘፀአት 27:10 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎችና ሃያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሰሶዎቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሃያ ምሰሶዎች፣ ሃያ የንሓስ መቆሚያዎች፣ የብር ኵላቦችና በምሰሶዎቹም ላይ ዘንጎች ይኑሩት። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሀያ ምሰሶዎቹና ሀያ እግሮቹ ከነሐስ የተሠሩ ይሁኑ፤ የምሶሶቹ ኩላቦችና ዘንጎች ከብር የተሠሩ ይሁኑ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ለእርሱም መደገፊያ ኻያ የነሐስ እግሮች ያላቸው ኻያ ምሰሶዎች ሥራ፤ በእነርሱም ላይ ከብር የተሠሩ ዘንጎችና ኩላቦች ይኑሩ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከናስ የተሠሩ ሀያ ምሰሶችና ሀያ እግሮች ይሁኑለት፤ የምሶሶቹም ኩላቦችና ዘንጎች የብር ይሁኑ። |
እንዲሁም በሰሜን ወገን መቶ ክንድ ርዝመት ያላቸው መጋረጃዎች፥ ከናስ የተሠሩ ሃያ ምሰሶዎች፥ ሃያም እግሮች ይሁኑ፤ ለምሰሶዎችም በብር የተለበጡ ኩላቦችና ዘንጎች ይሁኑ።
“ለድንኳኑም አደባባይ ሥራ፤ ከጥሩ በፍታ የተሠሩ የአደባባዩ መጋረጃዎችም በደቡብ በኩል ይሁኑ። የአንዱም ወገን ርዝመት መቶ ክንድ ይሁን፤
አምስቱንም ምሰሶዎች፥ ኵላቦቻቸውንም አደረጉ፤ ጉልላቶቻቸውንና ዘንጎቻቸውንም በወርቅ ለበጡአቸው፤ አምስቱም እግሮቻቸው የናስ ነበሩ።
ሃያውንም ምሰሶዎቻቸውንና ሃያውን እግሮቻቸውን ከናስ አደረገ፤ የምሰሶዎቹንም ኵላቦችና ዘንጎች ከብር አደረገ።
በአደባባዩ ዙሪያ ያሉትን እግሮች፥ የአደባባዩንም ደጃፍ እግሮች፥ የድንኳኑንም ካስማዎች ሁሉ፥ በአደባባዩ ዙሪያም ያሉትን ካስማዎች ሁሉ አደረገ።
ዐምዶቹም፥ የአንዱ ዓምድ ቁመት ዐሥራ ስምንት ክንድ ነበረ፥ የዙሪያውም መጠን ዐሥራ ሁለት ክንድ ነበረ፤ ውፍረቱም ጋት ያህል ነበረ፤ ባዶም ነበረ።