ዘዳግም 11:29 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር አምላክህ እግዚአብሔር በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፣ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) “ልትወርሳት ወደምትሄድባት ምድር ጌታ አምላክህ በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙን ደግሞ በጌባል ተራራ ላይ ታሰማለህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እግዚአብሔር ወደምትወርሳት ምድር በሚያስገባህ ጊዜ በረከቱን በገሪዛን ተራራ፥ መርገሙንም በዔባል ተራራ ታውጃለህ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) አምላክህም እግዚአብሔር ትወርሳት ዘንድ አንተን ወደምትሄድባት ምድር ባገባህ ጊዜ፥ በረከቱን በገሪዛን ተራራ መርገሙንም በጌባል ተራራ ታኖራለህ። |
ዮርዳኖስንም በተሻገራችሁ ጊዜ፥ ዛሬ እንዳዘዝኋችሁ፥ እነዚህን ድንጋዮች በጌባል ተራራ አቁሙ፤ በኖራም ምረጓቸው።
ይህንም ነገር ለኢዮአታም በነገሩት ጊዜ፥ ሄዶ በገሪዛን ተራራ ራስ ላይ ቆመ፤ ድምፁንም አንሥቶ አለቀሰ፤ እንዲህም አላቸው፥ “የሰቂማ ሰዎች ሆይ! ስሙኝ እግዚአብሔርም ይስማችሁ።