እስራኤልም ሁሉ ሕግህን ተላልፈዋል፤ ቃልህንም መስማትን እንቢ ብለዋል፤ በእርሱ ላይ ኀጢአት ሠርተናልና መርገምና በእግዚአብሔር ባሪያ በሙሴ ሕግ የተጻፈው መሐላ መጣብን።