ወደ አውራውም በግ ቀርቦ አየሁት፤ እርሱም ዘልሎ ወጣበት፤ አውራውንም በግ መታ፤ ሁለቱንም ቀንዶች ሰበረ፤ አውራውም በግ በፊቱ ሊቆም ኀይል አልነበረውም፤ እርሱም በምድር ላይ ጥሎ ረገጠው፤ አውራውንም በግ ከእጁ ያድን ዘንድ የሚችል አልነበረም።