ቀንዶችንም ተመለከትሁ፤ እነሆም፤ በመካከላቸው ሌላ ትንሽ ቀንድ ወጣ፤ በፊቱም ከቀደሙት ቀንዶች ሦስት ተነቃቀሉ፤ እነሆም በዚያ በትንሹ ቀንድ እንደ ሰው ዐይኖች የነበሩ ዐይኖች፥ በትዕቢትም የሚናገር አፍ ነበሩበት።