በታላቅም ሠራዊት ሆኖ ኀይሉንና ልቡን በአዜብ ንጉሥ ላይ ያስነሣል፤ የአዜብም ንጉሥ በታላቅና በብዙ ሠራዊት ይበረታል፤ ነገር ግን ዐሳብ በእርሱ ላይ ይፈጥራሉና አይጸናም።