ኤርምያስንም ባዩት ጊዜ ብዙ ድንጋይ ይዘው ወደ እርሱ ሮጡ፤ እርሱም ምስክርነቱን ጨረሰ፤ ባሮክና አቤሜሌክም መጥተው ቀበሩት፤ ያንም ድንጋይ አምጥተው በመቃብሩ አፍ እንደ መዝጊያ አድርገው አኖሩት።