ሕዝቡም ይህን ነገር በሰሙ ጊዜ ኤርምያስ፥ “የአምላክን ልጅ አምላክን አየሁት” ብሎ ስለ ተናገረው ስለዚህ ነገር ተቈጡ፤ እነሆም፥ “በኢሳይያስ እንዳደረግን በእርሱም እናድርግበት፤ ተነሡ” አሉ። እኩሌቶቹ፥ “በደንጊያ ወግረን እንግደለው እንጂ አይሆንም” አሉ።