ኤርምያስም “ንስሓ ግቡ፤ እነሆ፥ የጽድቅ መልአክ ይመጣል፤ ለብዙ ዘመንም ወደምትኖሩበት ቦታችሁ ይመልሳችኋል” ብሎ ወደ እነርሱ ላከ። እነርሱም ደስ ብሏቸው ስለ ሕዝቡ መሥዋዕት እየሠዉ ሰባት ቀን ተቀመጡ።