2 ሳሙኤል 23:11 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሴሜይ ነበረ። ፍልስጥኤማውያንም በቴሪያ ተሰበሰቡ። በዚያም ምስር የሞላበት የእርሻ ክፍል ነበር፤ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ከርሱም ቀጥሎ የሃራራዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ሌሒ በተባለ ስፍራ ምስር በሞላበት አንድ ዕርሻ ላይ በአንድነት ተሰብስበው ሳሉ፣ የእስራኤል ሰራዊት ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ከእርሱም ቀጥሎ የሃራርታዊው የአጌ ልጅ ሻማ ነበር፤ ፍልስጥኤማውያንም ምስር በሞላበት ሌሒ በተባለ ስፍራ አንድ እርሻ ላይ በአንድነት ተሰብስበው ነበር። ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ከሦስቱ ኀያላን ሦስተኛው ደግሞ የሃራር ተወላጅ የሆነው ዝነኛው የአጌ ልጅ ሻማ ነበር፤ አንድ ቀን ፍልስጥኤማውያን የምስር ማሳ ባለበት በሌሒ ተሰልፈው ነበር፤ እስራኤላውያንም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ከእርሱም በኋላ የአሮዳዊው የአጌ ልጅ ሣማ ነበረ። ፍልስጥኤማውያንም ምስር በሞላበት እርሻ በአንድነት ሆነው ተካማችተው ነበር፥ ሕዝቡም ከፍልስጥኤማውያን ፊት ሸሹ። |