አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
2 ሳሙኤል 13:35 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ኢዮናዳብም ንጉሡን፥ “እነሆ፥ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል፤ አገልጋይህ እንዳለው እንዲሁ ሆኖአል” አለው። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ኢዮናዳብም ዳዊትን፣ “እነሆ፣ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል፤ አገልጋይህም እንዳለው ሆኗል” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ዮናዳብም ለንጉሡ፥ “እነሆ፥ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል፤ አገልጋይህም እንዳለው ሆኖአል” አለው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዮናዳብም ዳዊትን “ልክ እኔ አገልጋይህ እንዳልኩት እነሆ፥ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል፤” አለው። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ኢዮናዳብም ንጉሡን፦ እነሆ፥ የንጉሡ ልጆች መጥተዋል፥ ባሪያህ እንዳለው እንዲሁ ሆኖአል አለው። |
አቤሴሎምም ኰበለለ። ጕበኛውም ጐልማሳ ዐይኑን ከፍ አደረገ፤ እነሆም፥ ብዙ ሰዎች በኋላው በተራራው አጠገብ በመንገድ ሲመጡ አየ። ጕበኛውም መጥቶ ለንጉሡ እንዲህ ብሎ ነገረው፥ “ብዙ ሰዎች በተራራው ጎን ባለው በአርኖን መንገድ ሲመጡ አየሁ።”
ተናግሮም በጨረሰ ጊዜ እነሆ፥ ወዲያው የንጉሥ ልጆች ገቡ፤ ድምፃቸውንም ከፍ አድርገው አለቀሱ፤ ደግሞም ንጉሡና ብላቴኖቹ ሁሉ እጅግ ታላቅ ልቅሶ አለቀሱ።