አድርአዛርም ልኮ በካላማቅ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን ሰበሰባቸው፤ ወደ ኤላምም መጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶቤቅ በፊታቸው ነበረ።
2 ሳሙኤል 10:17 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ለዳዊትም ነገሩት፤ እስራኤልንም ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፤ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ዳዊት ይህን በሰማ ጊዜ፣ መላውን እስራኤልን ሰብስቦ፤ ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ኤላም ሄደ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ለዳዊት ይህ በተነገረው ጊዜ፥ መላውን እስራኤልን ሰበሰበ፤ ከዚያም ዮርዳኖስን ተሻግሮ ወደ ዔላም ሄደ። ሶርያውያንም ለጦርነት ተሰልፈው ዳዊትን በግንባር ገጠሙት፤ አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ዳዊትም ይህን በሰማ ጊዜ የእስራኤላውያንን ወታደሮች ሁሉ በአንድነት አሰባስቦ የዮርዳኖስን ወንዝ ተሻገረ፤ ከዚያም ሶርያውያን ወደ ሰፈሩበት ወደ ሔላም ሄደ፤ ሶርያውያንም በሰልፍ ወጥተው በዳዊት ላይ ጦርነት ከፈቱ፤ መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ዳዊትም በሰማ ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፥ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ ወደ ኤላም መጣ፥ ሶርያውያንም በዳዊት ፊት ተሰልፈው ከእርሱ ጋር ተዋጉ። |
አድርአዛርም ልኮ በካላማቅ ወንዝ ማዶ የነበሩትን ሶርያውያን ሰበሰባቸው፤ ወደ ኤላምም መጡ፤ የአድርአዛርም ሠራዊት አለቃ ሶቤቅ በፊታቸው ነበረ።
ሶርያውያንም ከእስራኤል ፊት ሸሹ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ሰባት መቶ ሰረገለኞችን፥ አርባ ሺህም ፈረሰኞችን ገደለ፤ የሠራዊቱንም አለቃ ሶቤቅን መታ፤ እርሱም በዚያ ሞተ።
ዳዊትም በተነገረው ጊዜ እስራኤልን ሁሉ ሰበሰበ፤ ዮርዳኖስንም ተሻግሮ መጣባቸው፥ ከእነርሱም ጋር ተዋጋ፤ ዳዊትም ከሶርያውያን ጋር ተዋጋ፥ እነርሱም ከእርሱ ጋር ተዋጉ።