La Biblia Online

Anuncios


Toda la Biblia A.T. N.T.




2 ነገሥት 4:43 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

ሎሌ​ውም፥ “ይህን እን​ዴት አድ​ርጌ ለመቶ ሰው አቀ​ር​ባ​ለሁ?” አለ። እር​ሱም፥ “ይበ​ላሉ፥ ያተ​ር​ፋ​ሉም ብሎ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ተና​ግ​ሮ​አ​ልና ይበሉ ዘንድ ለሕ​ዝቡ ስጣ​ቸው” አለው።

Ver Capítulo

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

አገልጋዩም፣ “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው አቀርባለሁ?” ሲል ጠየቀ። ኤልሳዕ ግን፣ “እንዲበሉት ለሰዎቹ ስጣቸው፤ እግዚአብሔር፣ ‘በልተው ይተርፋቸዋል’ ይላልና” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው።

Ver Capítulo

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

አገልጋዩ ግን “ይህ ለመቶ ሰው የሚበቃ ይመስልሃልን?” ሲል ጠየቀው። ኤልሳዕም “እንዲበሉ አቅርብላቸው፤ በልተው መጥገብ ብቻ ሳይሆን እንደሚተርፋቸውም እግዚአብሔር ተናግሮአል” አለው።

Ver Capítulo

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

ሎሌውም “ይህን እንዴት አድርጌ ለመቶ ሰው እሰጣለሁ?” አለ። እርሱም “‘ይበላሉ ያተርፋሉም፤’ ብሎ እግዚአብሔር ተናግሮአልና ይበሉ ዘንድ ለሕዝቡ ስጣቸው፤” አለ።

Ver Capítulo



2 ነገሥት 4:43
15 Referencias Cruzadas  

በፊቴ ያለ​ቅ​ሳ​ሉና፦ የም​ን​በ​ላ​ውን ሥጋ ስጠን ይላ​ሉና ለዚህ ሕዝብ ሁሉ የም​ሰ​ጠው ሥጋ ከየት አለኝ?


እግ​ዚ​አ​ሔ​ርም ሙሴን፥ “በውኑ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እጅ አት​ች​ል​ምን? አሁን ቃሌ ይፈ​ጸም ወይም አይ​ፈ​ጸም እንደ ሆነ እነሆ፥ አንተ ታያ​ለህ” አለው።


ሁሉም በልተው ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሙሉ አነሡ።


ሁሉም በሉና ጠገቡ፤ የተረፈውንም ቁርስራሽ ሰባት ቅርጫት ሙሉ አነሡ።


ሰባቱን እንጀራስ ለአራት ሺህ በቈረስሁ ጊዜ፥ ቍርስራሹ የሞላ ስንት ቅርጫት አነሣችሁ? እነርሱም “ሰባት” አሉት።


ደቀ መዛሙርቱም “በዚህ በምድረ በዳ እንጀራ ከየት አግኝቶ ሰው እነዚህን ማጥገብ ይችላል?” ብለው መለሱለት።


እርሱ ግን፥ “እና​ንተ የሚ​በ​ሉ​ትን ስጡ​አ​ቸው” አላ​ቸው፤ እነ​ር​ሱም፥ “ለዚህ ሁሉ ሕዝብ የሚ​በቃ ምግብ ልን​ገዛ ካል​ሄ​ድን ከአ​ም​ስት እን​ጀ​ራና ከሁ​ለት ዓሣ በቀር ሌላ በዚህ የለ​ንም” አሉት።


ሁሉም በል​ተው ጠገቡ፤ ያነ​ሡ​ትም የተ​ረ​ፈው ቍር​ስ​ራሽ ዐሥራ ሁለት መሶብ ሞላ።


“አም​ስት የገ​ብስ እን​ጀ​ራና ሁለት ዓሣ የያዘ ብላ​ቴና በዚህ አለ፤ ነገር ግን እነ​ዚህ ይህን ለሚ​ያ​ህል ሰው ምን ይበ​ቃሉ?”