1 ሳሙኤል 3:5 - የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ወደ ዔሊም ሮጠ፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለው። እርሱም፥ “አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው። ሄዶም ተኛ። አዲሱ መደበኛ ትርጒም ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፣ “እነሆኝ የጠራኸኝ” አለው። ዔሊ ግን፣ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ወደ ዔሊም ሮጦ በመሄድ፥ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለው። ዔሊ ግን፥ “እኔ አልተጣራሁም፤ ተመልሰህ ተኛ” አለው፤ እርሱም ሄዶ ተኛ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ወደ ዔሊ ዘንድ ሮጦ በመሄድ “ስለ ጠራኸኝ እነሆ! መጥቻለሁ” አለ። ዔሊ ግን “እኔ አልጠራሁህም፤ ተመልሰህ ሂድና ተኛ” አለው፤ ሳሙኤልም ተመልሶ ተኛ። መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት) ወደ ዔሊም ሮጠ፦ እነሆኝ የጠራኸኝ አለው። እርሱም፦ አልጠራሁህም፥ ተመልሰህ ተኛ አለው። ሄዶም ተኛ። |
እግዚአብሔርም ደግሞ፥ “ሳሙኤል! ሳሙኤል” ብሎ ጠራው። ሳሙኤልም ተነሥቶ ዳግመኛ ወደ ዔሊ ሄደና፥ “እነሆኝ ስለ ጠራኸኝ መጣሁ” አለ። እርሱም፥ “አልጠራሁህም ተመልሰህ ተኛ” አለው።