መዝሙር 76:3 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም በዚያም ተወርዋሪውን ፍላጻ፣ ጋሻንና ሰይፍን፣ ጦርንም ሰበረ። ሴላ መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ድንኳኑ በሳሌም፥ ማደሪያውም በጽዮን ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም በዚያም የሚያንጸባርቁ ፍላጻዎችን፥ ጋሻና ጦርን፥ ሌሎችንም የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ሰባበረ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) እግዚአብሔርን ዐሰብሁት፥ ደስ አለኝም፤ ተናገርሁ፥ ነፍሴም ፈዘዘች። የጠላቶቼን ሁሉ ሰዓቶች ዐወቅኋቸው |
ኢዮሣፍጥና ሰዎቹም ምርኳቸውን ለማጋዝ ሄዱ፤ በዚያም መካከል እጅግ ብዙ መሣሪያና ልብስ፣ ሊሸከሙ ከሚችሉትም በላይ ውድ ዕቃዎችን አገኙ። ምርኮውም ከመብዛቱ የተነሣ ለመሰብሰብ ሦስት ቀን ፈጀ።
እግዚአብሔርም መልአክ ልኮ በአሦር ንጉሥ ሰፈር ተዋጊዎችን፣ መሪዎችንና የጦር መኰንኖችን እንዲያጠፋቸው አደረገ። ስለዚህ ንጉሡ በውርደት ወደ ገዛ አገሩ ተመለሰ። ወደ አምላኩ ቤተ ጣዖት እንደ ገባም፣ የገዛ ልጆቹ በሰይፍ ገደሉት።