መዝሙር 5:6 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ሐሰት የሚናገሩትን ታጠፋቸዋለህ፤ ደም የተጠሙትንና አታላዮችን፣ እግዚአብሔር ይጸየፋቸዋል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) በከንቱ የሚመኩ በዐይኖችህ ፊት አይኖሩም፥ ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላህ። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሐሰት የሚናገሩትን ሁሉ ታጠፋለህ፤ ነፍሰ ገዳዮችንና አታላዮችን ትጸየፋለህ። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ሐሰትን የሚናገሩትን ሁሉ ትጥላቸዋለህ፤ ደም አፍሳሹንና ሸንጋዩን ሰው እግዚአብሔር ይጸየፋል። |
መንግሥቱን የወሰድህበትን የሳኦልን ቤተ ሰው ደም ሁሉ እግዚአብሔር ወደ አንተው እየመለሰው ነው። እግዚአብሔር መንግሥትህን ለልጅህ ለአቤሴሎም አሳልፎ ሰጥቶታል፤ አንተ የደም ሰው ስለ ሆንህ እነሆ፣ መከራ መጥቶብሃል።”
በዚህ ጊዜ የቢክሪ ልጅ ስሙ ሳቤዔ የተባለ አንድ ምናምንቴ ብንያማዊ በዚያ ነበረ፤ እርሱም መለከት ነፍቶ እንዲህ ሲል ጮኸ፤ “እኛ ከዳዊት ድርሻ የለንም፤ ከእሴይም ልጅ ርስት የለንም፤ እስራኤል ሆይ፤ እያንዳንድህ ወደ ድንኳንህ ተመለስ!”
አንተ ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ክፉዎችን ወደ ጥፋት ጕድጓድ ታወርዳቸዋለህ፤ ደም የተጠሙ ሰዎችና አታላዮች፣ የዘመናቸውን እኩሌታ አይኖሩም። እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ።
በምድር ላይ የሚኖረውን ሕዝብ ስለ ኀጢአቱ ለመቅጣት፣ እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያው ወጥቶ ይመጣል፤ ምድር በላይዋ የፈሰሰውን ደም ትገልጣለች፤ የተገደሉትንም ከእንግዲህ አትሸሽግም።
በሁሉም ዐይነት ዐመፃ፣ ክፋት፣ ስግብግብነትና ምግባረ ብልሹነት ተሞልተዋል፤ ቅናትን፣ ነፍስ ገዳይነትን፣ ጥልን፣ አታላይነትንና ተንኰልን የተሞሉ ናቸው፤ ሐሜተኞች፣
ነገር ግን ፈሪዎች፣ የማያምኑ፣ ርኩሶች፣ ነፍሰ ገዳዮች፣ አመንዝሮች፣ አስማተኞች፣ ጣዖት አምላኪዎች፣ ውሸተኞች ሁሉ ዕጣ ፈንታቸው በዲንና በእሳት ባሕር ውስጥ መጣል ይሆናል። ይህም ሁለተኛው ሞት ነው።”