የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ተራራ ስትደርስም እግሩ ላይ ተጠመጠመች፤ ግያዝ ሊያስለቅቃት ሲመጣ፣ የእግዚአብሔር ሰው ግን፣ “እጅግ ዐዝናለችና ተዋት! እግዚአብሔር ይህን ለምን ከእኔ እንደ ሰወረውና እንዳልነገረኝ አልገባኝም” አለ።
መዝሙር 109:22 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም እኔ ድኻና ችግረኛ ነኝና፤ ልቤም በውስጤ ቈስሏልና። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) እኔ ችግረኛ ምስኪንም ነኝና፥ በውስጤም ልቤ ቆስሎአል። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም እኔ ድኻና ምስኪን ነኝ፤ የደረሰብኝም መከራ ልቤን አቊስሎታል። |
የእግዚአብሔር ሰው ወዳለበት ተራራ ስትደርስም እግሩ ላይ ተጠመጠመች፤ ግያዝ ሊያስለቅቃት ሲመጣ፣ የእግዚአብሔር ሰው ግን፣ “እጅግ ዐዝናለችና ተዋት! እግዚአብሔር ይህን ለምን ከእኔ እንደ ሰወረውና እንዳልነገረኝ አልገባኝም” አለ።
በሰዎች የተናቀና የተጠላ፣ የሕማም ሰውና ሥቃይ ያልተለየው ነበር። ሰዎች ፊታቸውን እንደሚያዞሩበት ዐይነት፣ የተናቀ ነበር፤ እኛም አላከበርነውም።
የጌታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ጸጋ ታውቃላችሁና፤ በርሱ ድኽነት እናንተ ባለጠጎች ትሆኑ ዘንድ እርሱ ሀብታም ሆኖ ሳለ ለእናንተ ሲል ድኻ ሆነ።