ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀምር። አትፍራ፤ ተስፋም አትቍረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋራ ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም።
ምሳሌ 15:5 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም ቂል የአባቱን ምክር ይንቃል፤ መታረምን የሚቀበል ግን አስተዋይነቱን ያሳያል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) ሰነፍ የአባቱን ተግሣጽ ይንቃል፥ ዘለፋን የሚቀበል ግን አእምሮው የበዛ ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ሞኝ የአባቱን ምክር ይንቃል፤ ተግሣጽን የሚቀበል ግን አስተዋይ ነው። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) አላዋቂ ልጅ የአባቱን ተግሥጽ ያቃልላል፤ ተግሣጽን የሚጠብቅ ግን ዐዋቂ ነው። እውነት ከበዛ ዘንድ ብዙ ኀይል አለ፥ ኀጢአተኞች ግን ከምድር ገጽ ይጠፋሉ፥ |
ደግሞም ዳዊት ልጁን ሰሎሞንን እንዲህ አለው፤ “እንግዲህ በርታ፤ ጠንክር፤ ሥራውንም ጀምር። አትፍራ፤ ተስፋም አትቍረጥ፤ እግዚአብሔር አምላኬ ከአንተ ጋራ ነውና፤ እርሱም የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ አገልግሎት ሥራ እስኪፈጸም ድረስ አይተውህም፤ አይጥልህም።
“አንተም ልጄ ሰሎሞን ሆይ፤ እግዚአብሔር ልብን ሁሉ ስለሚመረምርና ሐሳብን ሁሉ ስለሚያውቅ፣ የአባትህን አምላክ ዕወቅ፤ በፍጹም ልብና በበጎ ፈቃድ አገልግለው። ከፈለግኸው ታገኘዋለህ፤ ከተውኸው ግን እርሱም ለዘላለም ይተውሃል።
ጻድቅ ሰው ይቅጣኝ፤ ይህ በጎነት ነው፤ ይገሥጸኝም፤ በራሴ ላይ እንደሚፈስስ ዘይት ነው፤ ራሴም ይህን እንቢ አይልም። ጸሎቴ ግን በክፉዎች ተግባር ላይ ነው።