ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ እኮ ከንጉሡ ዐሥር እጅ ድርሻ አለን፤ ከዚህም በተጨማሪ በዳዊት ላይ ከእናንተ ይልቅ እኛ የበለጠ መብት አለን፤ ታዲያ እኛን የናቃችሁን ስለ ምንድን ነው? ንጉሣችን እንዲመለስ በመጀመሪያ የጠየቅነው እኛ አይደለንምን?” አሉ። ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር።
ምሳሌ 15:1 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የለዘበ መልስ ቍጣን ያበርዳል፤ ክፉ ቃል ግን ቍጣን ይጭራል። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የለዘበች መልስ ቁጣን ትመልሳለች፥ ሸካራ ቃል ግን ቁጣን ታስነሣለች። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም ልዝብ አነጋገር ቊጣን ያስታግሣል፤ የቊጣ አነጋገር ግን ቊጣን ያባብሳል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) ቍጣ ጥበበኞችን ታጠፋለች፤ የለዘበ ቃል ቍጣን ይመልሳል፥ ሻካራ ቃል ግን ጠብን ያነሣሣል። |
ከዚያም የእስራኤል ሰዎች ለይሁዳ ሰዎች፣ “እኛ እኮ ከንጉሡ ዐሥር እጅ ድርሻ አለን፤ ከዚህም በተጨማሪ በዳዊት ላይ ከእናንተ ይልቅ እኛ የበለጠ መብት አለን፤ ታዲያ እኛን የናቃችሁን ስለ ምንድን ነው? ንጉሣችን እንዲመለስ በመጀመሪያ የጠየቅነው እኛ አይደለንምን?” አሉ። ነገር ግን የይሁዳ ሰዎች የሰጡት መልስ የእስራኤል ሰዎች ከሰጡት መልስ ይልቅ እጅግ የከረረ ነበር።
እነርሱም፣ “ዛሬ አንተ ለዚህ ሕዝብ አገልጋይ ብትሆን፣ ብትገዛለትና ደስ የሚያሰኝ መልስ ብትሰጠው፣ ምን ጊዜም አገልጋይህ ይሆናል” ብለው መለሱለት።