ምሳሌ 10:16 - አዲሱ መደበኛ ትርጒም የጻድቃን ደመወዝ ሕይወት ታስገኝላቸዋለች፤ የክፉዎች ትርፍ ግን ቅጣትን ታመጣባቸዋለች። መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ) የጻድቅ ደመወዝ ለሕይወት ነው፥ የክፉ ገቢው ግን ለኃጢአት ነው። አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም የደግ ሰው መልካም ሥራ ሕይወትን ያስገኝለታል፤ የክፉ ሰው ኃጢአት ግን ቅጣትን ያስከትልበታል። የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ) የጻድቃን ሥራ ሕይወትን ያደርጋል፤ የኃጥኣን ፍሬ ግን ኀጢአት ነው። |
ለሚጠፋ እንጀራ አትሥሩ፤ ነገር ግን የሰው ልጅ ለሚሰጣችሁ ለዘላለም ሕይወት ለሚኖር ምግብ ሥሩ፤ ለዚህም እግዚአብሔር አብ ማረጋገጫ ማኅተሙን በርሱ ላይ ዐትሟልና።”
ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፤ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ፤ ምክንያቱም ለጌታ የምትደክሙት በከንቱ እንዳልሆነ ታውቃላችሁ።